Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ፍጹም አሰፋ ከመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደ መድረክ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 76ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፕላን እና ልማት ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በጎንዮሽ በተካሄደ መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በመድረኩም ፥ በኢትዮጵያ ባለፉት አስር ዓመታት ድህነትን ቅነሳ ላይ የተሠሩ ሥራዎችን አንስተዋል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎን በልማት እቅዶች ትግበራ፣ ቁጥጥር እና ግምገማ ላይ ጉድለት ሆኖ ታይቷል ስላሉት የስኬት ብያኔ እና ልኬትን በማንሳት አስረድተዋል።
አገሪቱ ከድህነት ጋር በተገናኘ የምትጠቀምባቸውን መለኪያዎችም ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
አያይዘውም ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ ባደረገችው የአስር ዓመት እቅድ ላይ የተሻሻሉ መለኪያዎችን ለመተግበር ያላትን ፍላጎት የጠቀሱ ሲሆን፥ ሀገራዊ ዘርፈ ብዙ ድህነት መለኪያ በማቅረብ ረገድ ባለድርሻ አካላትን የማስተባበሩ ሚና እርሳቸው የሚመሩት ፕላን እና ልማት ኮሚሽን ላይ የሚወድቅ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
በዚህም ኮሚሽኑ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ከኦክስፎርድ ፑቨርቲ ኤንድ ሂዩማን ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ጋር በመተባባር የመጀመሪያውን ሀገራዊ ዘርፈ ብዙ ድህነት መለኪያ ማበልጸጉን ነው የተናገሩት፡፡
በማማከሩ ረገድም በብሄራዊ ደረጃ ከአስራ አንድ ተቋማት የተዋቀረ ኮሚቴ መቋቋሙንም ያመለከቱት ኮሚሽነር ፍጹም አሰፋ፥ ለዚህ ተፈጻሚነት የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት እና የኦክስፎርድ ፑቨርቲ ኤንድ ሂዩማን ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
37
Engagements
Boost Post
36
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.