Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታ የጋራ ግብረ-ሀይል አስታወቀ፡፡

ግብረ ሀይሉ በመስቀል አደባባይ የተከናወነው ሥነ-ሥርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ነዋሪዎች ላሳዩት ጨዋነት ለተሞላበት ቀና ትብብርና ሥነ-ሥርዓቱ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በፍፁም ሙያዊ ብቃት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላትና የፀጥታ የጋራ ግብረ-ሀይል ምስጋና አቅርቧል።

መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ በአዲስ መንግስት ፣በአዲስ ተስፋ አዲስ ምዕራፍ የምትጀምርበት ቀን ብሏል ግብረ ሃይሉ፡፡

የጋራ ግብረሀይሉ ከፌዴራል ፖሊስ፤ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት፤ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር አስቀድሞ ዕቅድ በማውጣት እና ህብረተሰቡን በማሰተባበር የተከናወኑት ተግባራት ውጤት ማስገኘቱም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.