Fana: At a Speed of Life!

ስንተባበር ሸክማችን ይቀላል-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍል ከተማ ወረዳ 8 በክረምት በጎ ፍቃድ እድሳት የተደረገላቸውን 69 የአቅመ ደካማ ቤቶች አስረክበዋል።

ይህን ተከትሎ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በተጠናቀቀው በጀት አመት 2 ሺህ 455 የአቅመ ደካሞችን እና አረጋውያንን ቤት አፍርሰን በማደስ እና እንደገና በመገንባት አስተላልፈናል ብለዋል።

እንዲሁም “50 ሎሚ ለ 50 ሰዉ ጌጡ” እንዲሉ ስንተባበር ሸክማችን ይቀላል፤ እርስ በእርሳችን በመረዳዳት “ከእኛ ድጋፍ ወጪ በሁለት እግራችሁ መቆም አትችሉም” ብለዉ ለሚታበዩ አካላት ጭምር የኖረ የመረዳዳት ኢትዮጵያዊ ባህላችንን ዳግም እናስመሰክራለን ነው ያሉት።

በቀጣይም በአሸባሪዉና የህወሃት ቡድን ከመኖሪያቸዉ ለተፈናቀሉ የወሎ አካባቢ ነዋሪዎች፣ በተፈጥሮ ድርቅ ለተጎዱ የቦረና አካባቢ ወገኖችን እንዲሁም ለመከላከያ ሰራዊት ጭምር አለኝታነታችንን እናስመሰክራለን ሲሉ አስፍረዋል፡፡

ለዚህም በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶችና ለመላዉ የከተማው ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.