Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ ለቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ያዘጋጀውን ሽልማት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ ባዋለው የአርሶ አደሮች የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑ አርሶ አደሮች ለመጀመሪያ ዙር ያዘጋጀውን ሽልማት ለባለ እድለኞች አበርክቷል።
ባንኩ የቁጠባ ሂሳቡን ያዘጋጀው የአርሶ አደሩን የቁጠባ ባህል ለማሳደግና የባንኩ የጀርባ አጥንት የሆነውን የገጠሩን አርሶ አደር ተደራሽ ለማድረግ እንደሆነ በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
በዚህ የአርሶ አደር የቁጠባ ሂሳብ አማራጭ በ10 ወር ብቻ ከ200 ሺህ በላይ ደንበኞችን በማፍራት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉ ተመላክቷል።
በመጀመሪያ ዙር የአርሶ አደር የቁጠባ ሂሳብ ደንበኛ ለሆኑ ባለእድለኞችም የእርሻ መሳሪያ ትራክተር፣ ሞተር ሳይክልና ሞባይል የተበረከተላቸው መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ባንኩ አሁን ላይ አጠቃላይ ሃብቱ 83 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን÷በ500 ቅርንጫፎቹ 81 ሚሊየን ደንበኞችን ማፍራት መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.