Fana: At a Speed of Life!

ነጋዴዎች መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ ለፀጥታ ሃይሉ ድጋፍ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ ነጋዴዎች መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ ለፀጥታ ሃይሉ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገለጹ፡፡

“እኛ በአሸባሪ ቡድኑ የሀሰት ወሬ የትውልድ ቦታችንን ለቀን የትም አንሄድም ያሉት ነዋሪዎቹ÷ ይልቁንም እየነገድን ለመላው የጸጥታ አካል የሚጠበቅብንን እያደረግንና እየደገፍን ነው” ብለዋል።

ግንባር ድረስ ለመዝመት ፍላጎት ቢኖረንም ለሰራዊቱ ስንቅ ማቀበል አንዱ የትግል አካል በመሆኑ እየሰራን ድጋፍ እያደረግን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ወጣቱ የመከላከያ የኋላ ደጀን በመሆን ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ ግንባር እንደሚገኝ የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ፥ በህዝቡ ዘንድ እየታየ ያለው ወኔ አሸባሪውን በአጭር ጊዜ በመደምሰስ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እና አንድነቷ እንድትመለስ ያስችላል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

“የሀሰቱን ወሬ ለምደነዋል፣ እኛ ጠንክረን በመስራት የኢትዮጵያን አንድነት እና ሰላም ለማረጋገጥ የበኩላችንን ሃላፊነት መወጣት አለብን” ሲሉም ገልጸዋል።

“ሞት የትም ቦታ ይሞታል፣ ትልቁ ክብር በተወለዱበት ስፍራ ታግሎ መሞት ነው፤ እኛ የደሴ ከተማ ነጋዴዎች የሽብር ቡድኑን መታገል እንጂ የትም መሸሽ አንፈልግም”፤ እኛ ተረጋግተን እየሰራን ነው፤ ቦታችን ትተን መቼም ቢሆን አንሸሽም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.