Fana: At a Speed of Life!

መታገል እየቻለ ትግሉን የሚመለከት ሰው መኖር የለበትም – የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ያለዓለም ፈንታሁን ÷ የሕዝቡን ማዕበል በመጠቀም አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ሙሉ በሙሉ እንዲደመሰስ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ባስተላለፈው የክተት ጥሪ መሰረት ÷ የዞኑ ሕዝብ ዳግም የትግል ስሜቱ ግሎ መቀጠሉን ተናግረው ÷ “በእኛ ግንባር በእማወራ ወይም በአባወራ ደረጃ ቢያንስ አንድ ሰው መውጣት እንዳለበት ተወስኗል” ብለዋል።

ሕዝቡ ያለ ጉትጎታ ለትግል የመሰለፍ ፍላጎት እንዳለው እንገነዘባለን ያሉት አስተዳዳሪው ÷ መታገል እየቻለ ግን ቤቱ ቁጭ ብሎ ትግሉን የሚመለከት ሰው መኖር የለበትም” ብለዋል።

ዞኑ ጠላትን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ሕዝባዊ ማእበል ማንቀሳቀስ መጀመሩንም ነው የገለጹት።

“ማንኛውም ዘማች ወታደራዊ አመራሩ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በመመራት ጠላት በሚመታበት ሁኔታ እንዲሆን ተወስኗል” ነው ያሉት አስተዳዳሪው።

በተለያየ ምክንያት ወደ ዘመቻው የማይሄዱ ሰዎች በከተሞችና በሚያስፈልጉ ቦታዎች ተመድበው ጸጥታን የማስከበር ተግባር እንደሚፈጽሙም ዋና አስተዳዳሪው አመላክተዋል።

የጠላት ፍላጎት አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ስለሆነ ጠላትን ከተወሰነ አካባቢ በማጥፋት በሚገኘው ድል መኩራራት ሳይሆን ጠላት ሙሉ በሙሉ የሚጠፋበት ግብ ተቀምጧል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.