Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ በውሃና ኢነርጂ አቅርቦት በጋራ ለመስራት ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ፣ በደቡብ ሱዳንና በሱዳን የዴንማርክ አምባሳደር ከሆኑት ኪራ ስሚዝ ጋር በውሃና ኢነርጂ አቅርቦት ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውሃና ኢነርጂ አቅርቦት ላይ የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ የሚቻልባቸውን አማራጮች ያነሱ ሲሆን÷ የዴንማርክ ባለሃብቶችን ሊያሳትፍ የሚችል እድል ስለመኖሩም ተወያይተዋል፡፡
በታዳሽ ሃይል ልማት ላይም ኤምባሲው የሚሰራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ጠይቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ፣ በደቡብ ሱዳንና በሱዳን የዴንማርክ አምባሳደር ኪራ ስሚዝ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ኢነርጂ ልማት በተለይም በአሰላ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ መንግስታቸው ብድር መስጠቱን አስታውሰው÷ ሌሎች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን መደገፋቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም በታዳሽ ሃይል፣ በውሃ አቅርቦትና አግልግሎት ላይ ከሚኒስቴሩ ጋር ለመስራት ያላቸውን እቅድ መግለጻቸውን ከቀድሞው የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.