Fana: At a Speed of Life!

በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አንደራደርም-የምእራብ ጉጂ ዞን ነዋሪዎች

 

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አንደራደርም’ ሲሉ የምእራብ ጉጂ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ነዋሪዎቹ በዞኑ ቡሌ ሆራ ከተማ ባላሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የአሸባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን አፍራሽ እንቅስቃሴ አውግዘዋል፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፤ ትውልዱ ከመቼውም ጊዜ በላይ አገር የማዳን ታሪካዊ ሀላፊነት ወድቆበታል።

አሸባሪው ህወሃት በንጹሐን ላይ የሚፈጽመውን ግፍ ለማስቆም የተባበረ ክንድ እንደሚያስፈልገው ገልጸው፤ ለዚህ ደግሞ በአገራቸው ሳይደራደሩ ቡድኑን ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል።

አገር ለማዳንና ንጹሃንን ለመታደግ ወደ ግንባር በመዝመት የሽብርተኛውን ህወሃት ጥቃት ለመቀልበስ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ምዕራባዊያን ጣልቃ በመግባት ለሽብርተኞች የሚሰጡትን ድጋፍና ከላላ እንዲያቆሙም ጠይቀዋል፤ኢትዮጵያውያን በአገራቸው እንደማይደራደሩ ከታሪክ መማር ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል።
“ሀገር ሲፈርስ ሰምቶ እንዳልሰማና አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ ወጣት የለም” ብለዋል።

አሸባሪው ህወሃት ወረራ ከፈጸመባቸው ክልሎች ሁሉም ትምህርት ወስዶ አሸባሪውን ለመደምሰስ መክተት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

አሸባሪው ህወሃት በስልጣን ዘመኑ በኦሮሞ ቄሮና ቀሬ ላይ ያደረሰው በደል መቼም ቢሆን የማይረሳና የሁሉም ጠላት መሆኑን በተግባሩ ያረጋገጠ መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀምበሩ አበበ በበኩላቸው “በጫናና ተጽእኖ ሀገር ለማፍረስ የቋመጠው ሽብርኛው ህወሃት አይሳካለትም” ፤ወጣቱ በአገር ላይ የተከፈተውን አደጋ በመቀልበስ ከአባቶቹ የተረከበውን አገር ጠብቆና ተንከባክቦ ለተተኪው ትውልድ እንዲያስረክብ መክረዋል፡፡

የዞኑ ህዝብ አገር ለማደን ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.