Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ለተቸገሩ ዜጎች ከ36 ሺህ ኩንታል በላይ እህል ተከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን የዝናብ እጥረት ባስከተለው ድርቅ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ከ36 ሺህ ኩንታል በላይ እህል መከፋፈሉን የኦሮሚያ አደጋ ስጋት ስራ አመራርና የልማት ኮሚሽን ገለጸ።
መንግስት በድርቁ ምክንያት በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ 100 ሚሊየን ብር መድቦ እየሰራ መሆኑም ተመልክቷል።
ከተመደበው ገንዘብ እስከአሁን 10 ሚሊየን ብር ለከብቶች መኖ፣ 20 ሚሊየን ብር ለውሃ አቅርቦት መዋሉን ምክትል ኮሚሽነር ገረመው ኦሊቃ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ከተመደበው ገንዘብ በተጨማሪ 30 ሚሊየን ብር ለውሃ አቅርቦት እና 20 ሚሊየን ብር ለሳር ግዥ እንዲውል መወሰኑን ገልጸዋል።
በቦረና ዞን 13 ወረዳዎች የተከሰተው ድርቅ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት እንዳላደረሰ ገልጸው፥ የተልተሌ ወረዳ በከፊል የዲሎ፣ የዲሬ እና አሬሮ ወረዳዎች ደግሞ በአብዛኛው የእንስሳት ጉዳት እንደደረሰባቸውም ነው የገለጹት።
በተጨማሪም በጉጂ፣ በቦረና፣ በምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ እና ባሌ እና ምስራቅ ባሌ አካባቢዎች የክረምት ዝናብ ባለመጣሉ መጠኑ ቢለያይም ድርቅ መከሰቱንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የጠቆሙት ።
እየተከፋፈለ ካለው የእህል አቅርቦት መካከል የብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን 25 ሺህ ኩንታል፥ ቀሪውን ደግሞ ህብረተሰቡ እና የክልሉ መንግስት መሸፈናቸውን አክለዋል።
የከብቶች መኖ አቅርቦትን በተመለከተም ከ193 ሺህ በላይ ቤል የሳር እስር በመንግስትና በተለያዩ አካላት ቀርቦ እየተከፋፈለ ነው ብለዋል።
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.