Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ አባላት የመዲናዋን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ ሌት ተቀን እየሰሩ መሆናቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላቱ በተለያዩ ግንባሮች ከሚያደርጉት ተጋድሎ ጎን ለጎን ከተማዋን ከወራሪው የጁንታ ተላላኪዎች እና ከሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ እየሰሩ እንደሚገኙ ተገለጸ።

በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተመድበው የሚሰሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት አሸባሪውን የህወሓት ቡድንና ተላላኪውን ሸኔን ለመደምሰስ ከሚያካሂዱት የህልውና ዘመቻ በተጨማሪ የአዲስ አበባን ሠላምና ፀጥታ ከጥፋት ሃይሎች ለመጠበቅ ሌት ተቀን እየሰሩ እንደሚገኙ ነው የገለጹት።

አሸባሪው የጁንታው ቡድን ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እስካልወጣ ድረስ የህልውናው ዘመቻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት አመራርና አባላቱ ÷ ለዘመቻው መሳካትም እስከህይወት መስዋእትነት ለመክፈል ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ህብረተሰቡም ለፀጥታ ሃይሉ የሚያደርገው እገዛ ለከተማዋ ፀጥታ ጉልህ ሚና እንዳለው የገለፁት የፖሊስ አባላቱ በቀጣይም የህብረተሰቡ እገዛ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ጠይቀዋል።

በአሸባሪው የጁንታ ቡድን የተከፈተውን ወረራ በመቀልበስ አገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየሰራን ነው ማለታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.