ኢትዮጵያ በጉልበት የመጡባትን ታሸንፋለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦሌ ክፍለ ከተማ ለሀገር ክብር ለሚዋደቀው መከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበውን ድጋፍ የማስረከብ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡
ክፍለ ከተማው በገንዘብ ከ 63 ነጥብ 4 እንዲሁም በአይነት ከ26 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አሰባስቦ ነው በዛሬው ዕለት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያስረከበው፡፡
የአይነት ድጋፉ 142 ሰንጋዎች፣ 167 በጎችና የተለያዩ የምግብ እና የመድኃኒት ግብአቶችን ያካተተ ነው።
ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ ወጣቶች፣ የቀድሞ ሠራዊት አባላት እና አመራሮች ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ሉዓላዊነቷ እና አንድነትቷ እንዲጠበቅ ልጆቷ በቆራጥነት ይሰራሉ ብለዋል።
አሸባሪው የህውሓት ቡድን በእብሪት እና በድፍረት ኢትዮጵያ እንድትፈርስ በቁም ቅዠት ውስጥ ገብቷል ያሉት ከንቲባዋ÷ ይህ ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅዠታቸው መቼም ቢሆን አይሳከላቸውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ በጉልበት የመጡባትን አካላት ታሸንፋቸዋለች፤ ለዚህ ደግሞ ታሪክ ምስክር ነው ያሉት ከንቲባዋ አሁንም አሸባሪው ሀይል በአማራና አፋር ድባቅ እየተመታ ነው ብለዋል።
በቆንጂት ዘውዴ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!