Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 22 ሰዎች በኮቪድ 19 ለሕልፈት ሲዳረጉ፤ 1 ሺህ 505 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት 22 ሰዎች በኮቪድ 19 አማካኝነት ለሕልፈት ሲዳረጉ፤ 1 ሺህ 505 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል እንዲሁም 999 ሰዎች ደግሞ በጽኑ መታመማቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-…

በኦክስጅን እጥረት ሳቢያ ታካሚዎችን ለመርዳት እየተቸገርኩ ነው – የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኦክስጅን እጥረት ሳቢያ ታካሚዎችን ለመርዳት እየተቸገረ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በተጨማሪም በሆስፒታሉ ያጋጠመውን የኦክስጅን አጥረት ተከትሎ ቀደም ሲል ለሌሎች ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አቅርቦት…

በህንድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በ24 ሰዓታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 2 ሺህ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ፡፡ በተጨማሪም በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ነው የተባለው፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥም 295…

ተጨማሪ  1 ሺህ 524 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ  7 ሺህ 346 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 524 ሰዎች ኮሮናቫይረስ  እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 245 ሺህ 155 ደርሷል።…

በህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ ኮቪድ 19 ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ200 ሺህ 739 ሰዎች በላይ ኮቪድ 19 እንደተገኘባቸው የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በአንድ ቀን በዚህ ቁጥር በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ሲገኙ በህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በሀገሪቱ…

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ደረጃ ለማወቅ በሃገር አቀፍ ደረጃ ጥናት ሊካሄድ ነው 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ በሃገር አቀፍ ድረጃ ጥናት ሊጀመር መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ በጥናቱ ላይ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጨምሮ የጤና ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅትና የበሽታ…

በሦስት ደቂቃ ውስጥ ዓይንን በማየት ኮቪድ 19ኝን የሚመረምር የሞባይል መተግበሪያ ተሰራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መሰረቱን ጀርመን ያደረገ ኩባንያ በሦስት ደቂቃ ውስጥ ዓይንን ፎቶ በማንሳት /ስካን/ በማድረግ ኮቪድ19ኝን የሚመረምር የሞባይል መተግበሪያ /አፕሊኬሽን/ መስራቱን አስታወቀ፡፡ ይህ ሦስት ደቂቃ ይወስዳል የተባለው መመርመሪያ 95 በመቶ ውጤታማ ነው…

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ያላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 741 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) - ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 83 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1 ሺህ 741 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 228,996 ደርሷል። በሌላ በኩል…

በድሬዳዋ ባለፉት ሳምንታት ኮቪድ 19 ከተመረመሩ ሰዎች ውስጥ 45 በመቶዎቹ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ሦስት ሳምንታት የኮቪድ ናሙና ከሰጡ ሰዎች ውስጥ 45 በመቶዎቹ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገለጸ፡፡ የከተማው ጤና ቢሮ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው…

በኮቪድ19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር የጤና አገልግሎቱ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነው – የጤና ሙያ ማህበራት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሙያ ማህበራት በኮቪድ19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሄዱ የጤና አገልግሎቱ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እንደሚሆን አመላካች መሆኑን አስታወቁ። የጤና ሙያ ማህበራት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከቅርብ ሳምንታት…