Fana: At a Speed of Life!

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራውን ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማሩን ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሰቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር  ከሰተ ለገሰ  እንደገለጹት  የመማር ማስተማሩን ሥራ የጀመሩት  ከሚጠበቁት 13 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ  አብዛኛዎቹን    በመቀበል ላይ መሆኑንና የቀሩትንም  እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል ።

ተማሪዎቹ  በመቀሌ ማህበረሰብና ተማሪዎች ህብረት አቀባበል እየተደረገላቸው  ከየካቲት 1 ቀን 2013ዓ.ም. አንስቶ  ትምህርታቸውን መከታተል መጀመራቸውን  አስታውቀዋል።

የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች ፣መኝታ ቤቶች፣ ምግብ ማብሰያና መመገቢያ አዳራሾችን የኮሮናን ለመከላከል ታሳቢ ባደረገ  መልኩ ቀድመው መሰናዳታቸውን  ዶክተር ከሰተ አስረድተዋል።

ከአንደኛ እሰከ ስድስተኛ ዓመት ድረስ የሚማሩት እነዚህ  ተማሪዎቹ የተቋሙን ህግና ሥርዓት አክብረው  ትምህርታቸውን መከታታል እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

ትምህርታቸው መከታተል ከጀመሩት መካከል ከደቡብ ክልል የመጣው የአዲሀቂ ካምፓሰ የሶሾሎጂ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ቸርነት ሽፈራው  ትምህርት በመጀመሩ መደሰቱን ገልጾ÷ በንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት በኩል ግን እጥረት ስላለ እንዲስተካከል አስተያየቱን ሰጥቷል።

የእኛ ተማሪዎች ህልም በሠላምና ፍቅር ትምህርታችንን  መከታተልና ተመርቀን ራሳችንና ሀገራችን መጥቀም ነው ያለው ደግሞ  የሁለተኛ ዓመት ሶሾሎጂ ተማሪ እንድሪስ አብዱ ነው።

ከኦሮሚያ ክልል የመጣው ተማሪ ጫላ ሳፋይ በበኩሉ ዩኒቨርሲቲው ለመማር ማስተማር የሚያስችል የግቢው መሠረተ ልማት  ማሟላቱን ገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.