Fana: At a Speed of Life!

መወገድ ያለባቸው የመንግስት ሀብቶች ንብረት ምዝገባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ መወገድ ያለባቸው የመንግስት ንብረት ምዝገባ ከሚያዝያ 4 እስከ ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ።

የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ሃጅ ኢብሳ ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ÷ለረጅም አመታት ያለ ስራ ተቀምጠው ለብክለት መንስኤ ሆነው ባክነው የተቀመጡ ንብረቶችን በሽያጭ አልያም በስጦታ ለማስወገድ እየተሰራ ነው።

በዚህም ትኩረት የሚደረግባቸው የንብረት አይነቶች የተለዩ ሲሆን÷ ከንጉሱ ዘመን አንስቶ ተገዝተው አገልግሎት ያቆሙ ተሽከርካሪዎች፣ ያለስራ የቆሙ ማሽነሪዎች ፣ ላፕቶፕ እና ኮምፒውተሮች፣ ብረታብረትና ቆርቆሮዎች፣ ፎቶኮፒ ማሽን እና ፕሪንተሮች እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

በመንግስት ተቋማቱ የሚገኙት እነዚህ ንብረቶች 1 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው መሆኑን የገለጹት ሃጅ ኢብሳ÷እስካሁን ንብረቶቹ መወገድ ባለመቻላቸው ሀገር ስትጎዳ መቆየቷን አንስተዋል።

በመሆኑም ንብረቶቹን ለማስወገድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከእነተጠሪ ተቋማቶቻቸው በምዝገባና በማስወገድ ሂደቱ ሚናቸውን እንዲወጡ የተለያዩ ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ከዚህ ቀደም 40 የሚደርሱ የመንግስት ተቋማት ጋር ውይይት ተካሂዷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በዛሬው እለትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ከ50 በላይ የመንግስት ተቋማትጋር ውይይት መካሄዱን አብራርተዋል።

በዚህ ረገድም የመንግስት ተቋማት የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በሀብታሙ  ተክለስላሴወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.