Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በአራት በመቶ ነፃ ቀዘፋ የውሃ ዋና ውድድር ኢትዮጵያ 4ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ጨዋታዎች በሴቶቹ ዘርፍ በተደረገው የአራት በመቶ ነፃ ቀዘፋ የውሃ ዋና ውድድር ኢትዮጵያ 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። አትሌቶቹ ርቀቱን ለመጨረስ 5 ደቂቃ 18 ሴኮንድ ከ96 ማይክሮ ሴኮንድ ወስዶባቸዋል። ግብፅ በርቀቱ የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በማሻሻል የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፤ አልጄሪያ እና ዚምባቡዌ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል።
Read More...

ራፋኤል ቤኒቴዝ ከሴልታ ቪጎ አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ራፋኤል ቤኒቴዝ ከስፔኑ ሴልታ ቪጎ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ተሰናብተዋል፡፡ የሊቨርፑልና የቼልሲ የቀድሞ አሰልጣኝ የነበሩት ቤኒቴዝ የላሊጋውን ቡድን በአሰልጣኝነት የተረከቡት ባለፈው ሰኔ ወር ነበር፡፡ ሴልታ ቪጎ በራፋኤል ቤኒቴዝ አሰልጣኝነት ወቅት ካደረጋቸው 28 የላሊጋ ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻለው 5ቱን…

41 ሀገራትን አቆራርጦ አዲስ አበባ የገባው የሠላም ተጓዥ ብስክሌተኛ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሞሮኮ ራባት የተነሳው ኮትዲቯራዊ የሠላም ተጓዥ ብስክሌተኛ ካቮሬ ካሪን 41 ሀገራትን አቆራርጦ 42ኛ መዳረሻው በሆነችው ኢትዮጵያ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን በስም ብቻ ያውቃት እንደነበር ያስታወሰው የሠላም ተጓዡ÷ በአዲስ አበባ በተመለከተው ሁሉ መደነቁን እና መደሰቱን ተናግሯል፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና…

የተከተልኩት የሩጫ ስልትና የአሰልጣኝ ድጋፍ ለድል አብቅቶኛል – አትሌት ፅጌ ዱጉማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውድደሩ የተከተልኩት የሩጫ ስልትና የአሰልጣኝ ድጋፍ ለድል አብቅቶኛል ስትል በግላስጎ የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር የ800 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ አትሌት ፅጌ ዱጉማ ተናገረች፡፡ አትሌቷ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረገችው ቆይታ÷ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መነሻውን ያደረገው የአትሌቲክስ ሕይወቷ ወደ ጥሩነሽ…

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቶተንሃም አስቶን ቪላን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጪ የተጫወተው ቶተንሃም አስቶን ቪላን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ። ለቶተንሃም ማዲሰን፣ ጆንሰን፣ ሰን ሆንግ-ሚን እና ወርነር ጎሎቹን አስቆጥረዋል። በሜዳው የተጫወተው አስቶን ቪላ በ65ኛው ደቂቃ ላይ ማክጊን በቀይ ካርድ ከሜዳው ወጥቶበታል።

ኢትዮጵያ 15ኛውን የመላው አፍሪካ ጨዋታ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የ2031ን 15ኛውን የመላው አፍሪካ ጨዋታ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች፡፡ ኢትዮጵያ ፍላጎቷን የገለፀችው ከ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ጎንለጎን በተካሄደ የአፍሪካ ጨዋታዎች ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ ከትናንትና በስቲያ የተከፈተው እና እስከ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው 13ኛው የመላ…

ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 10፡00 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የፋሲል ከነማን የድል ጎሎች ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት እና ናትናኤል ማስረሻ በጨዋታ አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተክትሎም አፄዎቹ ነጥባቸውን ወደ 29 ከፍ…