Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 15ኛውን የመላው አፍሪካ ጨዋታ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የ2031ን 15ኛውን የመላው አፍሪካ ጨዋታ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች፡፡

ኢትዮጵያ ፍላጎቷን የገለፀችው ከ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ጎንለጎን በተካሄደ የአፍሪካ ጨዋታዎች ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

ከትናንትና በስቲያ የተከፈተው እና እስከ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በጋና አክራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህ ጨዋታ ላይ 54 የአፍሪካ ሀገራት በ29 የስፖርት አይነቶች የሚሳተፉ ሲሆን ÷ኢትዮጵያም በዘጠኝ የስፖርት አይነቶች የምትወዳደር ይሆናል፡፡

ግብፅ የ2027ን የመላው አፍሪካ ጨዋታን እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

በሰለሞን በቀለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.