Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል። ረፋድ ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ መከላከያን 2 ለ 1 አሸንፏል። መከላከያ በተሾመ በላቸው ጎል ጨዋታውን መምራት ቢችልም፥ ሐዋሳ ከተማ በብሩክ በየነ እና ወንድአገኝ ሐይሉ ጎሎች 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል። ከሰአት በኋላ በተካሄደ ሁለተኛ ጨዋታ ደግሞ አዳማ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
Read More...

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 በማሸነፍ ለዋንጫ የሚያደርገውን ፉክክር አጠናክሯል፡፡ ምሳ ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ሙጅብ ቃሲም ለፋሲል ከነማ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሱራፌል ዳኛቸው ቀሪዋን አንድ ጎል በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል፡፡…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረፋድ ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የወልቂጤ ከተማን የአሸናፊነት ጎሎች÷ ዋህብ አዳምስ፣ በኃይሉ ተሻገር እና ጫላ ተሸታ አስቆጥረዋል፡፡ ክትፎዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ÷ ነጥባቸውን 35 በማድረስ ከሀዲያ…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር  ሊግ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ረፋድ ላይ በተደረገው ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር በመሱድ መሀመድ ጎል እስከ እረፍት መምራት ቢችሉም ከረፍት መልስ አበባየሁ አጂሶ ባሰቆጠሯቸው ጎሎች ወላይታ ዲቻ ሙሉ 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡ የጦና ንቦች…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ28ኛ ሳምንት በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ጨዋታውን ላደረገው ባህርዳር ከተማ መናፍ አወል ብቸኛዋ የማሸነፊያ ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡ የጣና ሞገዶቹ ዘሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 33 በማድረስ ከወራጅ ቀጠና ሸሽተዋል፡፡…

ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ የክለቦች ውድድር ኢትዮጵያን ይወክላሉ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 13፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ረፋድ በተደረገው ጨዋታ የፋሲልን የማሸነፊያ ጎሎች ሙጂብ ቃሲም ከዕረፍት መልስ አስቆጥሯል፡፡ አጼዎቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 55 ያደረሱ ሲሆን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት በማጥበብ በዋንጫ…