Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በውድድሩ ኢትዮጵያ በ4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሃስ በአጠቃላይ በ14 ሜዳልያ 5ኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል። በውድድሩ የመጨረሻ ቀን በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በ5 ሺህ ወንዶች ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች። ከዚህ ባለፈም 2 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳልያም በማጠናቀቂያው ቀን በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በእርምጃ ውድድር ማግኘቷ ይታወቃል።
Read More...

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። ዛሬ በተካሄዱ ውድድሮች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳልያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው እና ዘርፌ ወንድማገኝ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት የወርቅና የብር ሜዳልያዎችን አስገኝተዋል።…

አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድርን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን 38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር አሸነፉ፡፡ በውድድሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች…

ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ “አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተካሄደ። በክፍለ ከተማው መድሃኔአለም አደባባይ ላይ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳድሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። በዕለቱ…

ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ  በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄዷል፡፡ ሩጫው የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ታላላቅ አትሌቶች በተገኙበት ተካሂዷል ። የጎዳና ላይ ሩጫው 5 ኪሎ ሜትር መንገድ የሸፈነ ሲሆን፥ ገቢውም የቀድሞውን ዳሞታ አትሌቲክስ ቡድንን መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ሀገር ቤት ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ሰኔ 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር መልስ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል። ብሄራዊ ቡድኑ በሳምንታት ቆይታው በማላዊ 2 ለ 1 ቢሸነፍም ግብጽን 2 ለ 0 በማሸነፍ በግብ ክፍያ በልጦ የምድቡ አናት ላይ መቀመጥ ችሏል። ዋሊያዎቹ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው በፊት በማላዊዉ ካሙዙ ኤርፖርት የኢትዮጵያ የአየር መንገድ…

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሠናክል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሞሪሺየስ እተካሄደ በሚገኘው የ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ዛሬ በተደረገው የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች ውድድር አትሌት ሃይለማሪያም አማረ እና አትሌት ታደሰ ታከለ 1ኛ እና ሁለተኛ በመሆን የወርቅና የብር ሜዳልያ ለአገራቸው ማስገኘታቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው…