Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ከዕረፍት በተመለሰው ፕሪሚየር ሊግ አርባ ምንጭ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከዕረፍት መልስ ዛሬ ተካሂዷል። ረፋድ ላይ ሲዳማ ቡናን ከአርባ ምንጭ ከተማ ባገናኘው ጨዋታ አርባ ምንጭ አሸናፊ ሆኗል። ጨዋታው 2 ለ 1 ሲጠናቀቅ ኤሪክ ካፓይቶ ሁለቱን የማሸነፊያ ጎሎች ለአርባ ምንጭ ከተማ አስቆጥሯል። የሲዳማ ቡና ማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ በሳላዲን ሰዒድ ተቆጥሯል። ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-…
Read More...

በግብፅ የተመዘገበው ድል የብሄራዊ ቡድኑን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብፅ የተመዘገበው ድል የብሄራዊ ቡድኑን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  ቆይታውን በተመለከተ የቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኙ በመግለጫቸው ዋሊያዎቹ የግብፅን ብሄራዊ ቡድን  ከማሸነፍ…

ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በውድድሩ ኢትዮጵያ በ4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሃስ በአጠቃላይ በ14 ሜዳልያ 5ኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል። በውድድሩ የመጨረሻ ቀን በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በ5 ሺህ ወንዶች ውድድር ሁለት የወርቅ…

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። ዛሬ በተካሄዱ ውድድሮች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳልያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው እና ዘርፌ ወንድማገኝ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት የወርቅና የብር ሜዳልያዎችን አስገኝተዋል።…

አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድርን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን 38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር አሸነፉ፡፡ በውድድሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች…

ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ “አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተካሄደ። በክፍለ ከተማው መድሃኔአለም አደባባይ ላይ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳድሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። በዕለቱ…

ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ  በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄዷል፡፡ ሩጫው የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ታላላቅ አትሌቶች በተገኙበት ተካሂዷል ። የጎዳና ላይ ሩጫው 5 ኪሎ ሜትር መንገድ የሸፈነ ሲሆን፥ ገቢውም የቀድሞውን ዳሞታ አትሌቲክስ ቡድንን መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።…