Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በዳሬሰላም ለሚካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ስፍራው አቀና

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ለሚካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ ከ20 እና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የአትሌቶች ልዑክ ዛሬ ማለዳ ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ የልዑካን ቡድኑ÷ 27 አትሌቶችን ያካተተ መሆኑን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉት አትሌቶችም÷ ከ100 ሜትር ጀምሮ እስከ 5 ሺህ ሜትር እንዲሁም የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ በአጠቃላይ በ20 የውድድር አይነቶች በሁለቱም ፆታ የሚካፈሉ ይሆናል፡፡
Read More...

የዓለም ዋንጫ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2022ቱ የኳታር የዓለም እግር ኳስ ውድድር አስቀድሞ በተለያዩ ሀገራት ለእይታ የሚቀርበው የዓለም ዋንጫ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ብራዚላዊው የባርሴሎና የቀድሞ የቀኝ መስመር ተከላካይ በጁሊያኖ ቤሌቲ ዋንጫውን ይዞ አዲስ አበባ ገብቷል። ዋንጫው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት…

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል። ከባህር ዳር ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደረገው ሲዳማ ቡና ጨዋታውን 3 ለ 1 አሸንፏል። ጊት ጋትኩት፣ ይገዙ ቦጋለ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ የሲዳማን የድል ጎሎች አስቆጥረዋል። አሊ ሱሌማን ደግሞ የባህር ዳር ከተማን ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል። ቀትር…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በባህር ዳር ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኦኪኪ ኦፎላቢ በ3ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ፋሲል ከነማ ወሳኝ 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡ አፄዎቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ…

በዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 ዳይመንድ ሊግ በእንግሊዝ በርሚንግሃም ከተማ ተካሂዷል። በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። በዚህም ዳዊት ስዮም 14:47:15 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ሌላዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሃዊ ፈይሳ 14:48.94…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ግንቦት 13፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ24ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል፡፡ ከሀዋሳ ከተማ ጋር የተጫወተው ኢትዮጵያ ቡና 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን የድል ጎሎች አላዛር ሽመልስ እና አማኑኤል ዮሃንስ እንዲሁም ዳግም ተፈራ በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥር ብሩክ በየነ የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ ጎል…

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በናይጄሪያ አቻው ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 12፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በናይጄሪያ አቻው 1ለ 0 ተሸንፏል፡፡ ዛሬ ቡድኑ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር የመጀመርያ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከናይጄሪያ አቻው ጋር አድርጓል፡፡ በጫዎታውም የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በናይጄሪ አቻው 1ለ 0 ተሸንፏል፡፡