Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። ዛሬ በተካሄዱ ውድድሮች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳልያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው እና ዘርፌ ወንድማገኝ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት የወርቅና የብር ሜዳልያዎችን አስገኝተዋል። በተመሳሳይ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ አትሌት ኃ/ማርያም አማረ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አምጥቷል፡፡ ረፋድ ላይ በተካሄደ የ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድርም…
Read More...

አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድርን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን 38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር አሸነፉ፡፡ በውድድሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች…

ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ “አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተካሄደ። በክፍለ ከተማው መድሃኔአለም አደባባይ ላይ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳድሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። በዕለቱ…

ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ  በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄዷል፡፡ ሩጫው የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ታላላቅ አትሌቶች በተገኙበት ተካሂዷል ። የጎዳና ላይ ሩጫው 5 ኪሎ ሜትር መንገድ የሸፈነ ሲሆን፥ ገቢውም የቀድሞውን ዳሞታ አትሌቲክስ ቡድንን መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ሀገር ቤት ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ሰኔ 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር መልስ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል። ብሄራዊ ቡድኑ በሳምንታት ቆይታው በማላዊ 2 ለ 1 ቢሸነፍም ግብጽን 2 ለ 0 በማሸነፍ በግብ ክፍያ በልጦ የምድቡ አናት ላይ መቀመጥ ችሏል። ዋሊያዎቹ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው በፊት በማላዊዉ ካሙዙ ኤርፖርት የኢትዮጵያ የአየር መንገድ…

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሠናክል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሞሪሺየስ እተካሄደ በሚገኘው የ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ዛሬ በተደረገው የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች ውድድር አትሌት ሃይለማሪያም አማረ እና አትሌት ታደሰ ታከለ 1ኛ እና ሁለተኛ በመሆን የወርቅና የብር ሜዳልያ ለአገራቸው ማስገኘታቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው…

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅና የብር ሜዳልያዎች አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅና የብር ሜዳልያዎች አገኘች። ሜዳልያዎቹ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የተገኘ ነው። በውድድሩ አትሌት ሞገስ ጥኡማይ እና አትሌት ጭምዴሳ ደበላ ተከታትለው በመግባት ለሃገራቸው ሜዳልያዎቹን ማስገኘታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደራሽን መረጃ ያመላክታል።…