Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ዋልያዎቹ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ከጊኒ ጋር ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ከጊኒ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡ ጨዋታው ዛሬ ምሽት 4፡00 ላይ በራባት ልዑል ሞውላይ አብደላ ስታዲየም ይደረጋል፡፡ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሰጡት መግለጫ÷ ከሚሊዮን ሰለሞን ውጭ ሌሎች ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ለጨዋታውም ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኝ ውበቱ ማረጋገጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ቀደም ሲል ባደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በጊኒ አቻው 2 ለ…
Read More...

አትሌት መዲና ኢሳ ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት መዲና ኢሳ ዛሬ የተካሄደውን ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር አሸነፈች፡፡ እንዲሁም ፅጌ ገብረ ሰላማ ሁለተኛ፣ መልክናት ውዱ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡ ለአንደኛ ደረጃ 70 ሺህ ብር፣ ለሁለተኛ ደረጃ 45 ሺህ ብር እንዲሁም ለሦስተኛ ደረጃ 30 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱ…

ባየርን ሙኒክ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማንን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ እግር ኳስ ክለብ ባየርን ሙኒክ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማንን ከአሰልጣኝነት ማሰናበቱን አስታውቋል። ክለቡ ወጣቱን አሰልጣኝ ለውጥ ፍለጋ በሚል እንዳሰናበታቸው ደይሊ ሜይል አስነብቧል። የቀድሞው የቦሩሲያ ዶርትመንድ፣ ፒ ኤስ ጂ እና ቼልሲ አሰልጣኝ የነበሩት ቶማስ ቱሼል የባቫሪያኑን ክለብ ይረከባሉ ተብሎ…

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል፡፡ የ38 ዓመቱ አጥቂ ትናንት ምሽት ሀገሩ ፖርቹጋል ሌችተንስታይንን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ በመሰልፍ ሁለት ጎሎችን በቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡ በጨዋታው መሰለፉን ተከትሎ ሮናልዶ ለሀገሩ 197 ጨዋታዎችን…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ዛሬ ምሽት ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ምሽት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ በካዛብላንካ መሐመድ 5ኛ ስታዲየም የሚደረገው ጨዋታ ምሽት 5፡30 የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ መርሐ ግብሩን ለማከናወን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን…

ሜሱት ኦዚል ጫማ መስቀሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል በ34 አመቱ ከእግር ኳስ ዓለም ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡ በጀርመኖቹ ሻልከ 04 እና ዌርደር ብሬመን የተጫወተው ኦዚል በ2010 የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ከጀርመን ብሄራዊ ቡድን ጋር ባሳየው ድንቅ ብቃት የስፔኑን ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ መቀላቀል ችሏል፡፡…

የኢትዮጵያ አጭር፣ መካከለኛ፣ 3ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ 3ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ ለአትሌቶች የውድድር እድል መፍጠር እንዲሁም የክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦችና ተቋማት አትሌቶች…