Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ዋልያዎቹ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ሩዋንዳን 1ለ0 አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሩዋንዳን 1ለ0 አሸንፏል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ 10 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አካሂዷል፡፡ በጨዋታውም ዋልያዎቹ 1ለ0 አሸንፈዋል፡፡ ግቡን ከነዓን ማርክነህ በ83ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2023 በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከጊኒ ጋር በሞሮኮ…
Read More...

ስፖርት ማህበራዊ ግንኙነት የሚጠናከርበት መድረክ ነው- አምባሳደር  መስፍን ቸርነት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ስፖርት ማህበራዊ ግንኙነት የሚጠናከርበት የዲፕሎማሲ መድረክ ነው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት ተናገሩ፡፡ 8ኛው የመላ አማራ ስፖርት ውድድር  በጎንደር ከተማ በይፋ ተጀምሯል። በዚህ ወቅት የባህልና ስፓርት ሚኒስትር  ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት እንዳሉት÷ ስፖርት በትውልድና…

በሶል ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የ77ኛው ሶል ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ርቀቱን አጠናቀዋል፡፡ በውድድሩ አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ26 ሴኮንድ በመግባት ቀዳሚ ሲሆን ፥ አትሌት ሺፈራው ታምሩ እና…

በ ጅቡቲ ኢንተርናሽናል ሚት የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) ለስድስተኛ ጊዜ በተካሄደው 'ጅቡቲ ኢንተርናሽናል ሚት' የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች አሸንፈዋል፡፡ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች አለሽኝ ባወቀ 16 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰኮንድ በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት አጠናቃለች። እንዲሁም አዳኔ አንማው 16 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ከ66 ማይክሮ ሰከንድ…

በቻምፒየንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ ማንቼስተር ሲቲን ከባየር ሙኒክ ያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በድልዱሉ መሰረት የአምናው ሻምፒዮን ሪያል ማድሪድ ከቼልሲ ጋር ተገናኝቷል። የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ደግሞ ከፖርቹጋሉ ቤኔፊካ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። የእንግሊዙን ማንቼስተር ሲቲ ከጀርመኑ ሃያል ባየርን ሙኒክ ጋር ያገናኘው ጨዋታ የሩብ ፍጻሜው ተጠባቂ…

ክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራን አሰናበተ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራን ማሰናበቱን አስታወቀ። ክለቡ ፈረንሳዊውን የቀድሞ የአርሰናል አማካይ ከውጤት ማጣት ጋር በተያያዘ ከአሰልጣኝነት እንዳሰናበተው ቢቢሲ አስነብቧል። የደቡብ ለንደኑ ክለብ ባለፉት 12 ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። በፕሪሚየር ሊጉም ከ27 ጨዋታዎች 27…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ18ኛ ሳምንት ጀምሮ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ሊግ ካምፓኒው አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አህጉራዊ ውድድር ምክንያት የተቋረጠው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እስከ 17ኛ ሳምንት ድረስ በድሬዳዋ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በቀጣይ ውድድሩ የሚካሄድበትን ከተማ…