Fana: At a Speed of Life!

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የአፍሪካ ቱሪዝም የዓመቱ ጀግና ሴት ተብለው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የፈረንጆቹ 2019 ምርጥ የአፍሪካ ቱሪዝም መሪ ሆነው ተመረጡ፡፡

ምርጫውን ይፋ ያደረገው በጋና የሚገኘው ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን የተሰኘው ድርጅት ነው ተብሏል፡፡

ሽልማቱ ከአስር ቀናት በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

ዶክተር ሂሩት በቱሪዝም፣ በሆቴልና መስተንግዶ በአጠቃላይ በዘርፉ ላይ ለተሰማሩ እና ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራኞተችና አመራር በሙሉ እውቅናው የእናንተ ነውና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

“እጅ ለእጅ ተያይዘን ከሰራን ገና ሩቅ እንጓዛለን በማለትም” በማህበራዊ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.