Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ መንግስት የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኬንያ መንግስት የላፕሴት ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገልጿል።

የላፕሴት ኮሪደር ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሚኒስትር ሜና አኬንዶ በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ጉብኝት በማድረግ ከአምባሳደር መለስ ዓለም ጋር ተወያይተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው የኢትዮጵያ እና የኬንያ የግል ባለሀብቶች የላሙን ወደብ መጠቀም እንዲችሉ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የወደቡ አገልግሎት በተመለከተም በኢትዮጵያ የማስተዋወቅ ሥራ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ኃላፊው ጠቁመዋል።

አምባሳደር መለስ ዓለም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ኢትዮጵያ እና ኬንያን የበለጠ ማስተሳሰር የሚችሉ ሶስት ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

እነዚህም የላሙ ወደብ ምርቃት፣ የሞያሌ የአንድ ኬላ አገልግሎት ሥራ መጀመር እና የኬንያው ሰፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃድ ማግኘት ዋና ዋናዎች እንደሆኑ አምባሳደር መለስ አሰረድተዋል።

የኬንያ ባለሀብቶችም በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የኢንቨስትመንት እድል እንዲጠቀሙ በማድረግ የላሙን ወደብ አገልግሎት ማስተዋወቅ ያስችላል ብለዋል።

ሁለቱም ወገኖች በላሙ እና በሞያሌ የጉብኝት ፕሮግራሞችን ለማመቻቸት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.