ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በሁለተዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው ላይ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ሁለቱ መሪዎች ተናግረዋል::
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡