Fana: At a Speed of Life!

200 ዓመታትን ያስቆጠረው በህንድ የሚገኝ መስጊድ በከባድ ዝናብ ጉዳት ደረሰበት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊህ የሚገኘው 200 ዓመታትን ያስቆጠረው መስጊድ በከባድ ዝናብ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰበት ተነገረ።

ከቀይ የሸክላ ድንጋይ በፈረንጆቹ 1823 ዓ.ም እንደተገነባ የሚነገረው መስጊዱ በከተማዋ ከሚገኙ ጥቂት ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው።

በትናትናው ዕለት በከተማዋ የተከሰተው ጎርፍ ለ2 ሰዎች ምክንያት ሲሆን በርካታ ቤቶች ደግሞ ፈርሰዋል።

የ45 ዓመቱ የመስጊዱ ኢማም መሀመድ ዛሂድ መስጊዱ በፈረሰበት ወቅት በመስጊዱ ውስጥ በሚገኘው የመኝታ ክፍሌ ተኝቼ ነበር ያሉ ሲሆን ከፍተኛ ድምፅም ተሰምቷል ሲሉ ለአናዶሉ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

በአሁን ወቅት መስጊዱ ዝግ ቢሆንም ከመስጊዱ ውጭ ባለ ስፍራ ፀሎት እና ሀይማኖታዊ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.