የመጨረሻዎቹ የዴሞክራሲ ገንቢ እና ጠባቂዎች ራሳችን ኢትዮጵያውያን እንጂ ወዳጆቻችን አይደሉም -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል ፕሬዚዳንቶችና ከምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር ሳምንታዊ የምርጫ ቅድመ ዝግጅትን ገምግመዋል።
በውይይቱም የመራጮች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑ ተብራርቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷ እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ዜጎች በተራዘመው የምዝገባ ጊዜ ተጠቅማችሁ የምርጫ ካርድ እንድትወስዱ አበረታታለሁ ብለዋል ።
በምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ አካላት ምደባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በቀጣይ ሳምንታት የሚሰማሩ ይሆናልም ነው ያሉት ።
የመጨረሻዎቹ የዴሞክራሲ ገንቢ እና ጠባቂዎች ራሳችን ኢትዮጵያውያን እንጂ ወዳጆቻችን አይደሉም ብለዋል።
ባለቤት ይወስናል፤ ወዳጅ ደግሞ ያግዛል። የምርጫው ሂደት ስኬታማ እና ሰላማዊ እንዲሆን በጋራ እንሥራ ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!