ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ማዳበሪያ ለማምረት ተፈራረሙ
በስምምነቱ መሰረት የአገር ውስጥ ሀብቶችን በመጠቀም የኢትዮጵያ ጋዝ እና ሞሮኮ ፎስፎሪክ አሲድ በድሬዳዋ የተቀናጀ የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ይቋቋማል።
በየጊዜው እያደገ የመጣውን የማዳበሪያ ፍላጎትን በዋናነት “ዩሪያ እና ኤን ፒ ኤስ+” ለማሟላት ይህ ፕሮጀክት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል።
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2022 ወደ አገር ውስጥ የምታስገባው ማዳበሪያ 1 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ሲሆን፥ ይህ ቁጥር በ2030 ደግሞ 2 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል።