Fana: At a Speed of Life!

ከአሸባሪው ህወሃት ጀርባ ያለው የውጪ ኃይል ጫና በተባባሪ ፕሮፌሰር ሊ ሺንጋንግ ዕይታ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሌሎች ሥራዎቹን ሁሉ ወደ ጎን ገፍቶ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ብቻ ሙሉ ትኩረቱን በማድረግ የተለያዩ ማዕቀቦችን እና ጫናዎችን ለመጫን ክፍተት እየፈለገ ይመስላል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ዘርፍ የፈፀመቻቸው ማሻሻያዎች የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስበዋል፡፡

ህወሓት ሥልጣን ላይ በነበረ ጊዜ ኢትዮጵያ ያላየቻቸውን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ነፃነቶች እንዲሁም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ሳትፈታ የቆየችውን የድንበር ጉዳይ በሠላም በመፍታቷ የተገኘው ስኬት የህወሃትን ደስታ የቀማ መሆኑን ሺን ሚን ኒውስ አመላክቷል፡፡

የእሲያ እና የምሥራቃዊ ቋንቋዎች እና ባሕሎች ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሊ ሺንጋንግ፥ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት የሚከተለው ከሁሉም ሀገራት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚጋብዝ ፖሊሲ የበርካታ ሀገራትን ቀልብ ስቧል ይላሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያና የቻይና ጠንካራ ወዳጅነት በተለይም “በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” ቻይና በአፍሪካ የፈጠረችው ተጽዕኖ አሜሪካ በቀጣናው ላይ እራሷን እንድትቆጥብ አድርጓታል፡፡

ይህም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ መፈጸም የፈለገችውን እስትራቴጂያዊ ፖሊሲ ነጥላ በማግለል መፈጸም እንዳትችል መንገድ ዘግቶባታል ነው ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር ሊ ሺንጋንግ፥ አሜሪካ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ የሚያስችላትን ነገሮች ሁሉ ስታማትር እንደነበረ ገልጸው፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሁኔታውን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳወቅ እና ለአሸባሪው ቡድን ከለላ በመስጠት ግጭቱን ለማባባስ እና ኢትዮጵያን ለማስፈራራት ተጠቅማበታለች ነው ያሉት፡፡

እንደ ሊ ሺንጋንግ ÷ “የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የዘር ማጥፋት እየፈጸመ ነው” በማለትም አሜሪካ ግጭቱን ለማባባስ እና የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ ተጠቅማበታለች፡፡

ምንም እንኳን ጉዳዩ በተባበሩት መንግስትታት ድርጅት ተቋማት እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጋራ ጥናት የዘር ማጥፋት እንዳልተፈጸመ ቢረጋገጥም ፥ አሜሪካ ግን ኢትዮጵያን ለማሽመድመድና ለአሜሪካ እንድትንበረከክ ለማድረግ አጎዋን ጨምሮ የተለያዩ ማዕቀቦችን ጥላለች ፤ አሸባሪው ቡድንም እንዲያንሰራራ በተዘዋዋሪ ሰርታለች ሲሉም ሁኔታውን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የአሜሪካ ፍላጎት እንዲሳካ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ግስጋሴውን በመቀጠል በርካታ ቦታዎችን መያዝ አለበት ፤ የዐቢይ መንግስት ደግሞ ግጭቱን መቆጣጠር ተስኖት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ዘንድ ተሰሚነትን ማጣት አለበት ብለዋል፡፡ አሁን ላይ ግን ይህ ከቅዠት ባለፈ ሊሆን እንደማይችል ሺን ሚን ኒውስ ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ አመላክተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.