Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን በመስጊዶችና ፖለቲከኞች ላይ ጥቃት ለመፈፀም አሲረዋል የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመስጊዶች፣ ፖለቲከኞች እና ጥገኝነት በጠየቁ አካላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም አሲረዋል የተባሉ የቀኝ ዘመም ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስራ ማዋሏን ጀርመን አስታወቀች።

የዴር ሃርቴ ኬርን ቀኝ ዘመም ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ 12 ተጠርጣሪዎች አርብ ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

የቡድኑ አባል ነው ተብሎ የተጠረጠረ ሌላኛው ግለሰብም በፍለጋ ላይ እንደሚገኝ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በጀርመን በተለይ በቀደመው ጊዜ የኮሚዩኒስት አስተዳደር በነበረበት ምስራቃዊ ክፍል የቀኝ ዘመም አራማጆች ሃሳብ እያቆጠቆጠ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አራቱ የዴር ሃርቴ ኬርን ቀኝ ዘመም ቡድንን በመመስረት የተጠረጠሩ ሲሆን፥ ስምንቱ ደግሞ ለቡድኑ የገንዘብ፣ የመሳሪያ እና ሌሎች ድጋፎችን በማቅረብ የተጠረጠሩ ናቸው።

ይህ የጀርመን ቀኝ ዘመም ቡድን በፊንላንድ ከአምስት ዓመት በፊት ከተመሰረተው ኦዲን ከተሰኘ ቀኝ ዘመም ወታደራዊ ቡድን ጋር ግንኙነት ሳይኖረው አይቀርም የሚል ጥርጣሬ አለ።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.