Fana: At a Speed of Life!

የጫካ ፈረሶች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸውና በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ በቁንዱዶ ተራራ ውስጥ የሚገኙት የጫካ ፈረሶች ዝርያቸው እንዳይጠፋ እየተሰራ ባለው ስራ ውጤት እየተገኘ መሆኑ ተገለፀ።
ከአንድ ምዕተ አመት በላይ እድሜ እንዳላቸው የሚነገርላቸው በቁንዱዶ ተራራ ላይ ያሉ ፈረሶች አሁን ላይ በተደረገላቸው ጥበቃና ክትትል ቁጥራቸው እንጨመረ መሆኑ ነው የተገለጸው።
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ ወይዘሮ አለይካ ነስረዲን፥ ከናሚቢያ ውጪ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የጫካ ፈረስ ዝርያዎች ቁጥራቸው በእጅጉ ተመናምኖ ከዚህ በፊት 4 ብቻ ቀርተው እንደነበር ተናግረዋል።
ይህ ቁጥር አሁን ላይ በተሰራ የጥበቃ ስራ ወደ 31 ሊያድግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የደንና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተጠሪ አቶ ዳውድ ሙሜ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ በሀገሪቷ ካሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ የቁንዱዶ የጫካ ፈረሶች ተጠቃሾቹ ናቸው ብለዋል።
ከፍተኛ ክትትልና ጥበቃ እንዲደረግላቸው በሚል እሳቤ ባለፈው አመት መገባደጃ ላይ ከፌዴራል መንግስት ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የብዝሃ ህይወት ኢንስቲቲዩት የሐረር ብዝሀ ህይወት ማእከል ዳሬክተር አቶ ሰለሞን መንግሥቱ፥ ከኦሮሚያ መንግስት የተረከቡትን የእንክብካቤ ስራ በማቀላጠፍ ፈረሶቹን ከተጋረጠባቸው የመጥፋት አደጋ ለመታደግ እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የፈረሶች መኖርና እየተመናመነ የመጣው ቁጥራቸው እንዲጨምር መደረጉ ለሀገሪቷ የቱሪዝም እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ስላለው ሁሉም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተመላክቷል።
የቁንዱዶ ተራራ በምስራቅ ሐረርጌ የጉርሱምና ጃርሶ ወረዳዎችን አካሎ የያዘ ሲሆን፥ በአካባቢውም የጫካ ፈረሶቹን ጨምሮ በርካታ የመህስብ ስፍራዎችን ይዟል።
በቲያ ኑሬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.