የአውሮፓ ህብረት በሊቢያ ላይ አዲስ የቁጥጥር ዘዴ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሊቢያ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለማስቆም አዲስ የቁጥጥር ዘዴ ለመዘርጋት ተስማሙ።
27 የህብረቱ አባል ሀገራት በቁጥጥር ዘዴው መርሆች ስምምነት ላይ የደረሱ ቢሆንም በፅሁፍ የተዘጋጀው የተልዕኮው ረቂቅ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል
“ዋናው ዓላማው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ነው” መሆኑን የሉክዘምበርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄን አሴልቦርን ተናግረዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠው የትሪፖሊ መንግስት አብዛኛውን ምስራቃዊ እና ደቡባዊ ሊቢያን በተቆጣጠረው የጄኔራል ካሊፋ ሀፍታር ኃይል ጥቃት እየደረሰበት ነው ተብሏል ፡፡
የአውሮፓ ህብረት የባህር እና የአየር ተልዕኮ ምስራቃዊ ሜዴትራኒያን ላይ በመሆን የቁጥጥር ስራውን እንደሚሰራ ተነግሯል።
የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉጂ ዲ ማዮ በበኩላቸው የህብረቱ መርከቦች ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንዲደርሱ ምክንያት ከሆነው ዘመቻው ይቋረጣል ብለዋል
ምንጭ፡-ቢቢሲ