Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የመሬት ልማት ማኔጅመንት የስራ ሀላፊ ግማሽ ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የመሬት አገልግሎት አስፈፃማለሁ በማለት ከግል ባለጉዳይ 500 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለው የመሬት ልማት ማኔጅመንት ኃላፊ አቶ ብርሐን ጌራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
 
የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ደመና ተስፋዬ ለየካ ኮሙኒኬሽን እንደገለፁት፥ግለሰቡ የይዞታ ጉዳይ አስፈፅማለሁ በማለት ከግል ተገልጋይ የ500 ሺህ ብር ቼክ ሲቀበል ከአንድ ግብረ አበሩ ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
 
ተጠርጥሪው በወረዳው ሀሮን ሆቴል አካባቢ 500 ሺህ ብር መጠን ከተፈረመነት የንብ ባንክ ቼክ ቁጥር 566322 ኤግዚቪትነት ጋር መያዙ ተገልጿል።
 
በ2013 ዓ.ም የተደረገውን የመሬት ማጥራትና የኦዲት ስራ ሽፋን በማድረግ የመከነ ካርታ አስተካክላለሁ በሚል ተጠርጣሪው ጉቦ መቀበሉንና እጅ ከፍንጅ መያዙን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
የወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አስራት አበራ÷ኃላፊው በወረዳው ስራ ከጀመረ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው ተናግረዋል፡፡
 
ከዚህ በፊት በወረዳ 8 አስተዳደር በመሬት ልማት ማኔጅመንት ባለሙያነትና በፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ኃብት ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊነት መስራቱንም አስታውሰዋል።
 
ከይዞታ ጋር የተያያዙ የመሬት አገልግሎቶች በጊዜያዊነት በከተማ አስተዳደሩ የታገዱ መሆኑ ይታወቃል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.