Fana: At a Speed of Life!

ማይክ ፖምፔዮ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት አስፈላጊነትን በተመለከተ መምከራቸው ነው የተገለጸው።

 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቀጣይ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ወሳኝ መሆኑን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
 
በቀጣይ የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥም ገንቢ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
 
በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተወያይተዋል።
 
በዚህ ሀገራቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ሀገራዊ ለውጥ ለመደገፍ ዝግጁ መሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.