Fana: At a Speed of Life!

19ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር የመክፈቻ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣የካቲት 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው አገር አቀፍ የባህል ስፖርት ውድድር እና  15ኛው የባህል ፌስቲቫ የመክፈቻ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በደብረብርሃን ከተማ  ተካሂዷል።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ  የባህልና ስፖርት ሚኒስትር  አቶ ቀጀላ መርዳሳን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ በውድድሩ  የሚሳተፉ  ክልሎች ባህላቸውን የሚያሳዩ  ልዩልዩ ትርዒቶችን ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡

አገር አቀፍ የባህል ስፖርትውድድሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 13ቀን 2014ዓ.ም በ10 የስፖርት ዘርፎች ነው የሚካሄደው።

 

በአበበ የሸዋልዑል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.