Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታግደዉ የነበሩ አገልግሎቶችን መስጠት ሊጀምር ነዉ

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀመሩ የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
ኤጅንሲዉ ከዚህ ቀደም በሃገር አቀፍ ደረጃ ከአዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ውጪ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከሰኞ የካቲት 14 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀመሩ መሆኑን አስታዉቋል፡፡
በመሆኑም በሁሉም ክፍለ ከተማ በየወረዳው በተዘጋጀ መርሃ ግብር ነዋሪው መስተናገድ የሚችል መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሌብነትን በመፀየፍ ፤ ስጋት እየሆነ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ በመስራት የሚደረግ ማጭበርበርን ማህበረሰቡ እንዲከላከልም ኤጀንሲዉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.