Fana: At a Speed of Life!

የፋይናንስ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከአውሮፓ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የፋይናንስ ሚኒስትር  አቶ አህመድ ሽዴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባኤ በተጓዳኝ ከአውሮፓ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ ዶ/ር አኒታ  ዌበር ጋር በብራስልስ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም  በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ውይይት በማካሄድ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ተነስተዋል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተለይም የመድሃኒት አቅርቦትን ተደራሽ ለማደረግ የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይም  ውይይት ተደርጓል።

መንግስት በወሰዳቸው አዎንታዊ እርምጃዎች በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ፍላጎት ማሳየቱን የገለፁት ሚኒስትሮቹ፥ የህወሓት የሽብር ቡድን የሚያደረገውን ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዝምታ ከመመልከት ወጥቶ ተጠያቂ ሊያደረገው እንደሚገባም ገልጸዋል።

መንግስት የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች አጋሮች ጋር  የሚያደርገውን ቀጣይ ውይይት ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚካሄድ አስረድተዋል።

በመጨረሻም በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመግባባት ላይ መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.