Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በዘጠኝ ወራት ከ43 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ43 ቢሊየን 157 ሚሊየን 43 ሺህ ብር በላይ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው በዘጠኝ ወራት ውስጥ 37 ቢሊየን 340 ሚሊየን 41 ሺህ ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ነው 43 ቢሊየን 157 ሚሊየን 43 ሺህ ብር መሰብሰብ የቻለው፡፡
በዚህም የዕቅዱን 115 ነጥብ 52 በመቶ መፈጸም መቻሉን ነው የሚያመላክተው፡፡
አፈጻጸሙ ከዕቅዱ አንጻር ሲነጻጸር የ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብልጫ ያሳየ ሲሆን÷ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ወይም 33 ነጥብ 56 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.