Fana: At a Speed of Life!

አንድነትና አብሮነትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድነትና አብሮነትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡
የፊቼ ጫምባላላ በዓልን በሚገባ ጠብቆ ለሚመጣው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም ርዕሠ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
ባህሉን ጠብቀው እዚህ ያደረሱትን የብሔሩ ተወላጆች አመስግነው÷ በተሻለና በደመቀ መልኩ ለማክበር በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ድህነት ለማሸነፍ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው÷ በዓሉ የተጣሉ የሚታረቁበት አብሮነት የሚጠነክርበትና ለሰው ልጆች ክብር የሚሰጥበት ነው ብለዋል፡፡
የአባቶች እውቀት ድንቅና አኩሪ ባህል መሆኑን፣ ተጋግዞና ተባብሮ ወደ ፊት መራመድ እንደሚያስፈልግና አንድነትና መቻቻልም የህዝቡ መገለጫ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
በዓሉ በቀጣይም ለ15 ቀናት የሚቀጥልና በተለያዩ ክዋኔዎች የሚከበር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በፊቼ ጫምባላላ በዓል ላይ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ሚኒስትሮች፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ከፌደራል እና ከክልሎች የመጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ታዳሚ ሆነዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ደረጃ ለማድረስ በልማት ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያቆመን አንዳች ሀይል አይኖርም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው÷ በዓሉ ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር ቆይቶ ዛሬ ላይ የደረሰ እና አመታትን ያስቆጠረ ጥንታዊ ስልጣኔ ነው ብለዋል፡፡

ፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ክልል ብቻ ሳይሆን የአለም ሀብት በመሆኑ ሊጠበቅና ሊለማ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያን ባህሎች መመዝገብና ማጥናት አስፈላጊ እንደሆነ ያነሱት ደግሞ÷ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ናቸው፡፡የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ደረጃ ለማድረስ በልማት ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያቆመን አንዳች ሀይል አይኖርም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው÷ በዓሉ ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር ቆይቶ ዛሬ ላይ የደረሰ እና አመታትን ያስቆጠረ ጥንታዊ ስልጣኔ ነው ብለዋል፡፡

ፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ክልል ብቻ ሳይሆን የአለም ሀብት በመሆኑ ሊጠበቅና ሊለማ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያን ባህሎች መመዝገብና ማጥናት አስፈላጊ እንደሆነ ያነሱት ደግሞ÷ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ናቸው፡፡

በብርሃኑ በጋሻው፣ ቢቂላ ቱፋ፣ በቤዛዊት ከበደ፣ ታመነ አረጋና ደብሪቱ በዛብህ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.