Fana: At a Speed of Life!

በመቱ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 29፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በመቱ ዮኒቨርሲቲ የምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ምርምርን ከሀገር በቀል እውቀት ጋር በማዋሀድ የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማረጋገጥ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው ስድስተኛው ጉባዔ ላይ ከመቱና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰባሰቡ 86 የምርምር ስራዎች ለውይይት ቀርበዋል።

በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የመቱ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር በድሉ ተካ ሳይንስን ከሀገር በቀል እውቀት ጋር ማዋሀድ የሚለው ሀሳብ የጉባዔው ዋነኛ ትኩረት መሆኑንና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በጉባዔው ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የሀገር በቀል እውቀት ተመራማሪው አብዱልፈታ አብዱ በበኩላቸው የሀገር በቀል እውቀትን ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለመጠቀም የሳይንሳዊ ቃላትን አረዳድ አተረጓጎም እና አሠራር ማስተካከል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የልማት ስራዎችን አካባቢውንና ሀገራዊ ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

የምርምር ጉባዔው ነገም ቀጥሎ ይውላል።

በማስረሻ ፍቅሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.