Fana: At a Speed of Life!

ፓዝ ፋይንደር ለሰሜን ወሎ ዞን ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በሰሜን ወሎ ዞን በጦርነቱ ለተጎዱ ጤና ተቋማት የሚውል ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል የአማራ ክልል ተወካይ አቶ ሀብታሙ አጥናፍ ÷ድርጅቱ በጦርነቱ የተጎዱና የወደሙ የጤና ተቋማትን ስራ ለማስጀመር የሚያግዙ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ በዞኑ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ለመደገፍ እንደሚሰራ የገለጹት ተወካዩ÷የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ በበኩሉ ÷ የተደረገው ድጋፍ በአሸባሪው እና ወራሪው የህወሓት ቡድን የወደሙ የጤና ተቋማትን ለማጠናከር ያግዛል ማለቱን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.