1 ሺህ 5 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 5 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ÷ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 5 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 51 ሕጻናት፣ 319 ሴቶችና 635 ወንዶች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና ክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል ተብሏል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ20 ሺህ 900 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡