Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን ተግባራዊነት በመከታተል በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል የነበረው የዲፕሎማሲ ግንኙነት፣ የተፈረሙ ስምምነቶችና በሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮች የአፈፃፀም ደረጃ በተመለከተ ከዘጠኝ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
በምክክር መድረኩ የስኳር ኮርፖሬሽን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የግብርና ምርምር ኢኒስቲቲዩት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በብራዚል የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጣፋ ቱሉና የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ኢየሩሳሌም አምደማርያም ከባለድርሻ አካላቱ ጋር በቀጣይ በቅንጅት በመስራት ሀገሪቱ ከብራዚል ጋር ባላት ግንኙነት የበለጠ ተጠቃሚ እንድትሆን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በመድረኩ የብራዚል-አፍሪካ ግንኙነት፣ ኢትዮጵያና ብራዚል በኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸው ትብብርና በሀገራቱ መካከል በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ፣ በአየር ትራንስፖርትና በማሪታይም አገልግሎት ወዘተ ዙሪያ የተፈረሙ ከ12 በላይ ስምምነቶች ያሉበት የአፈፃፀም ደረጃ እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች ተዳሰዋል።
ኢትዮጵያ ከብራዚል ጋር ባላት ግንኙነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች የበለጠ ተጠቃሚ መሆን እንድትችል በሁለቱ ሀገራት የተፈረሙ የስምምነቶች ተግባራዊነት በቅርብ በመከታተል የሚፈለጉ ድጋፎችን በመለየት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ መገለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.