አውስትራሊያ ከ41 ዓመታት በኋላ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አስተናገደች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አውስትራሊያ ከፈረንጆቹ 1981 ወዲህ አጋጥሟት የማያውቅ የዋጋ ግሽበት ማስተናገዷን የሀገሪቷ ስታቲስቲክስ ቢሮ አመላከተ፡፡
ሀገሪቷ በሚያዝያ ወር ያስመዘገበችው የዋጋ ግሽበት መጠን 7 ነጥብ 2 በመቶ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የሀገሪቷ ስታቲስቲክስ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር ቶቢያስ ቶማስ በሠጡት መግለጫ ÷ የነዳጅ እና የኃይል አቅርቦት ዋጋ መናር እና የምግብ ዋጋ መጨመር ለግሽበቱ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡
የአውስትራሊያ መንግስት ግሽበቱን ለመቋቋም በፈረንጆቹ መጋቢት ወር መጨረሻ ላይ 2 ነጥብ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ፈሰስ ማድረጉንና በጋዝ እና በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ላይም የግብር ማስተካከያ እርምጃዎች መውሰዱን ሺንዋ ዘግቧል፡፡