Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት የወደሙ ከ1 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል መርሐ ግብር በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የመልሶ ግንባታ መርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው የተጀመረው፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አቢ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷ በክልሉ ውድመት ከደረሰባቸው የትምህርት ተቋማት መካከል 170 ያህሉ በትምህርት ሚኒስቴር የሚገነቡ ናቸው፡፡

ከእነዚህ ተቋማት ውስጥ ሰባት ትምህርት ቤቶች በመጀመሪያው ዙር የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦላቸው በቅርብ ጊዜ ግንባታቸው የሚጠናቀቁ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

በአማራ ክልል በትምህርት ተቋማት ላይ ብቻ የደረሰው ጠቅላላ የጉዳት መጠን ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን÷ በደሴ ከተማ እና በደቡብ ወሎ ዞን በትምህርት ተቋማት ላይ የደረሰው የወድመት መጠን ደግሞ 1 ቢሊየን 729 ሚሊየን ብር ይገመታል ተብሏል፡፡

በእሸቱ ወልደሚካኤል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.