Fana: At a Speed of Life!

2ኛው ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ የፊታችን መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኮንፈረንሱ የሀገር መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሆቴል ባለቤቶች፣ አስጎብኝዎች፣ የምስራቅ አፍሪካ የዘርፉ መሪዎችና ባለሃብቶች፣ አምባሳደሮች፣ አማካሪ ድርጅቶች እና ሌሎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በፕሮግራሙ ከሚደረጉ ኮንፈረንሶች በተጨማሪ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላከታል።

በዚህ መሰረት የእግር ጉዞ፣ ጉብኝቶች፣ የምርትና ኢንቨስትመንት ትውውቅ ፕሮግራሞች፣ የእውቅና ስነ ስርዓቶችን ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶች ይካሄዳሉ።

ኮንፈረንሱን የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ከኢትዮጵያ ሆቴል አሰሪዎች ፌደሬሽን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ነው።

ኮንፈረንሱ የሀገር ውስጥ እና የሀዋሳ ከተማን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከማነቃቃት ባለፈ ሰላምና የዘርፉን ኢንቨስትመንት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.