Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይካሄዳል፡፡

18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአሜሪካ ኦሪገን መካሄዱን ቀጥሏል፡፡

በዚህም ዛሬ ሌሊት 10፡25 የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡

በሩጫ ውድድሩ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉት አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ ፣ ዳዊት ስዩም እና ጉዳፍ ፀጋይ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና የደረጃ ሰንጠረዥ እስካሁን ሶስት የወርቅ፣ አራት የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ ስምንት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች::

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.