Fana: At a Speed of Life!

በኦሪገን ኢትዮጵያ በጉዳፍ ፀጋይ 4ኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶቾ 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ለኢትዮጵያ 4ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች።

ዳዊት ስዩም ሶስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ውድድሩን ለተሰንበት ግደይ አምስተኛ በመውጣት አጠናቃለች።

በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ግሩም የቡድን ሩጫ አሳይተዋል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው እስከአሁን አራት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.