Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ ለግብር ከፋዮች የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለግብር ከፋዮችና ባለድርሻ አካላት የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡

የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ያዘጋጀው መርሐ ግብር “ግብር እከፍላለሁ፣ አስከፍላለሁ፣ ህልውናየንም አረጋግጣለሁ” በሚል መሪ ቃል ነው በአሶሳ ከተማ የተካሄደው፡፡

በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ÷ በ2015 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ገልጸዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት ከሚያደርጉት ጥረት በተጨማሪ በተለይ የንግዱ ማህበረሰብ ግብር የመክፈል ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው÷የታክስ አስተዳደር ዋነኛ ተልዕኮ ታማኝ ግብር ከፋዮችን የሚያበረታታ አሰራር መዘርጋት ነዉ ብለዋል፡፡

ግብር ሰብሳቢ ተቋማት ከሙስናና ብልሹ አሰራሮች በመፅዳት ለተገልጋዮች ምቹ የሆነ አገልግሎት  በመስጠት ግብር በወቅቱ እንዲከፈል የማድረግ ሃላፊነታቸዉን በሚገባ ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በበጀት አመቱ ክልሉ ከ1 ነጥብ 76 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ማቻሉን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መለሰ ክዊ ናቸው፡፡

በመርሐ ግብሩ ግብርን በታማኝነት በመክፈል ግዴታቸውን ለተወጡ ግብር ከፋዮችና ባለድርሻ አካላት እውቅና ይሰጣል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.